.

የትራፊክ ደህንነትን የማረጋገጥ ሥራ ለአንድ አካል የሚተው መሆን የለበትም

የመንገድ መጓጓዣው ዘርፍ በአንድ ሀገር ዕድገት ውስጥ ያለው ከፍተኛ ሚና እንዳለ ሆኖ ውጤታማና በጥንቃቄ ስራ ላይ ካልዋለ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ጨምሮ ሊያደርስ የሚችለው ጥፋት ከፍተኛ ነው፡፡ በየጊዜው እየሰፋ የመጣው የመንገድ ትራፊክ አደጋን ከግምት በማስገባት በዓለማችን በሽታዎችና አስጊና ድንገት ከሚከሰቱ የሰውን ህይወት በመቅጠፍ ከሚታወቁት የመንገድ ትራፊክ አደጋ አስረኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በ2012 እንደገለፀው በዚህ አደጋ ምክንያት በየዓመቱ 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ከ30 እስከ 50 ሚሊዮን  የሚገመቱ ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳተኝነት ይዳረጋሉ፡፡ በዚህ አደጋ ምንያት በየዓመቱ የሚደርስ የንብረት ውድመትም ከ600 ቢሊዮን  የአሜሪካ ዶላር በላይ እንደሚሆን ይህ መረጃ ገልጿል፡፡

እንደ ሀገራችንም በየጊዜው እየደረሰ ያለው የመንገድ ትራፊክ አደጋ አስጊ እየሆነ መጥቷል፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ላለፉት አምስት ዓመታት ከ1999 እሰከ 2003ዓ.ም ብቻ ከ51 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች በሞትና ለተለያዩ የአካል  ጉዳተኝነት ተጋልጠዋል፡፡ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ከሌሎች ክልሎች  ጋር ሲታይ የኦሮሚያ ክልል በመንገድ ትራፊክ አደጋ ግንባር ቀደም ደረጃ ላይ ካሉት ክልሎች አንዷ ናት፡፡

የትራፊክ አደጋ በኦሮሚያ ለምን ይበዛል መነሻውሰ ምን ይሆን ?

የኦሮሚያ ክልል በሀገሪቷ እንብርት ላይ የምትገኝና ከሀገሪቷ ስፋት ውስጥ 34.3%ን የሚሸፍን፣ እንዲሁም ከርዕሰ መዲናዋ ፊንፊኔ ወደ ሌላ ክልል ከተሞች የሚወስዱ ትላልቅ መንገዶች የሚያቋርጧት በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት የመንገድ ትራፊክ እንቅስቀሴ ከሌሎች ክልሎች ይበልጥ የሚስተናገድባትና ትራፊክ አደጋው ብዛትም በትራፊክ እንቅስቃሴው መጠን እየጨመረ መምጣቱ ግልፅ ሆኗል፡፡ ለዚህ አደጋ መነሻ የሆነው ደግሞ ከፍተኛ ፍጥነት፣ ያለ አግባብ ለመቅደም መሞከር፣ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ለብዙ ጊዜ ያለ እረፍት ማሽከርከርና የሌሊት ጉዞ ከፍተኞቹ ናቸው፡፡ የሚከሰቱት አደጋዎች ይበልጦቹ ከአሽከርካሪዎች ጥፋት እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ለክልሉ አስጊ እየሆነ የመጣውን የትራፊክ አደጋ ጉዳይ ለመቀነስ ምን እየተሰራ ነው ?

እየጨመረ የመጣውን አስጊ የክልሉ የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንና የኦሮሚያ የትራስፖርት ኤጀንሲ በቅንጅት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ የኦሮሚያ ክልል ትራነስፖረትን ለመወሰን በድጋሜ የወጣው ደንብ ቁጥር 143/2004 ስራ ላይ መዋል ጀምሯል፡፡ ከዚህም ሌላ በዘመናዊ መሳሪያዎች መቆጣጠር እንደ ራደር በመሳሰሉት መጠቀም የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ጠጥተው የሚያሽከረክሩ ሰዎችን የሚለይ አልኮል ቴስተር (alchol tester) ለመጠቀም በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ለህግ ተላላፊዎች በሚደረግ ቁጥጥር ብቻ እየደረሰ ያለውን አደጋ መቆጣጠር ስለማይቻል በመንገድ የሚጠቀም ህብረተሰብ የመንገድ አጠቃቀም ግንዛቤ አግኝቶ በዚህ ምክንያት ከሚደርስ አደጋ ራሱን እንዲጠብቅ ለሰፊው ህብረተሰብ በነዚህ አካላት እጠተሰጠ ያለው ትምህርት መሰረታዊ ለውጥ እያመጣ ነው፡፡  በተጨማሪም በሁለት ሳምንት አንዴ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ለአሽከርካርዎችና ለመንገደኞች የሚሰጠው ትምህርት አበረታች ነው፡፡ አደጋው የሚበዛባቸውን አከባቢዎች በመለየት መከላከል የሚቻልበት ሁኔታ ላይም እየተሰራ ነው፡፡ ትምህረት በመስጠቱ ስራ የተገኙ ውጤቶችም አበረታች ነው፡፡ በተሰጠው የመንገድ ትራፊክ ግንዛቤም መንገደኛው ግራውን ይዞ መሄድን ባህሉ እያደረገው መጥቷል፡፡በዚህ ረገድ ብዙ የኦሮሚያ ዞኖችን እንደ ምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡

በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንና በኦሮሚያ ትራንስፖርት ኤጀንሲ ይህን አደጋ ለመቀነስ እየተደረጋ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ቢሆንም በክልሉ እየደረሰ ያለው አደጋ አሁን እንኳን አስጊ ጉዳይ ስለሆነ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በሚደርሰው አደጋ ምክንያት በህይወትና ንብረት ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡ከዚህ በመነሳት የትራፊክ አደጋ በሀገር ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዕድገት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት መገመት አያስቸግርም፡፡

ይህ አደጋ የሚያደርሰው የህወትና ንብረት ጉዳት አስጊ ከመሆኑም ሌላ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ እየተፋጠነ ላለው ለሀገራችን ዕድገት እንቅፋት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን አደጋ በመቀነስ የመንገድ ጉዞ ደህንነትን ማረጋገጥ ለአንድ አካል ብቻ ሊተው የሚገባ ጉዳይ መሆን የለበትም፡፡ ስለዚህ አስጊና የእያንዳንዳችንን ቤት ማንኳኳት የሚችል ይህን ጉዳይ ለመቅረፍ ሁሉም ዜጋ ባለበት የመንገድ ትራፊክን ህግ በማክበርና በማስከበር የሚጠበቅበትን ድርሻ መወጣት አለበት፡፡

Go to top