የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ለህብረተሰቡ እየሰጠ ያለውን የፖሊስ ስራ አገልግሎት የበለጠ ዘመናዊ ለማድረግ በቅርቡ ዌብሳይት ከፍቶ በማስመረቅ አገልግት መስጠት ጀምሯል፡፡ በኮሚሽኑ ዌብሳይት የምረቃ ስነ-ስርዓት መድረክ ላይ በመገኘት መርቀው ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢብራሒም ሐጂ እንደ ገለጹት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የህብረተሰቡን ተሳትፎ በእጥፍ በማሳደግ ወንጀልንና የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ አስተማማማኝነት ያለው ሠላም በቀጣይነት ማረጋገጥ፣ህገ-መንግስቱንና የህግ የበላይነትን አክብሮ በማስከበር የስራ ግዴታውን ለመወጣት የህብረተሰቡ ተሳትፎና በቂ ማስረጃ፣ ጥራት ያለውና ወቅታዊ መረጃ ለአጠቃላይ የፖሊስ ስራ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ ተከፍቶ አገልግሎት መሰጠት የጀመረው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ዌብ ሳይት በተለያዩ አሰፈላጊ የፅሑፍ ርዕሶች የተደራጀ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ከኮሚሽኑ ዓላማና አመሰራረት አንስቶ የወንጀል መከላከልና የምርመራ ስራ እንቅስቃሴ፣ ኮሚኒኬሽን፣ የማህበረሰብ ፖሊስ አገልግሎት፣ የትራፊክ ደህንነት ማረጋገጥ ስራና ህብረተሰቡ ወንጀልንና የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የሚያደርገው የዘመቻ ስራ በፅሑፉ አብይ ቦታ ያላቸው ናቸው፡፡