የሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከኮሚሽን እስከ ወረዳ ደረጃ የስራ ሂደት ተደርጎ የተቋቋማ ሲሆን በሁሉም ደረጃ የማኔጅመንት ኮሚቴ ሆነው እየሰሩ ነው፡፡ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ፖሊስ ስለ ሴቶችና ህፃናት መብት እንዲሁም በፆታ እኩልነት ላይ ትልቅ ስራ እየሰራ ነው፡፡ሴቶች ከወንድ እኩል መስራት እንደሚችሉና ችሎታ እንዳላቸው፣ በንብረታቸው ላይ የባለቤትነት መብት እንዳላቸውና እኩል ውሳኔ መስጠት እንዳለባቸው ሰፊ ግንዛቤ ሲሰራ ቆይቷል አሁንም እየተሰራ ነው፡፡
በተለያየ ምክንያት የወንጀል ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች በወንጀል ምርመራና ፍትሕ ማሰጠት ዘርፍ እንዲሁም ከሌሎች የፍትሕ አካላት ቅንጅት ጋር መዝገቡ ተጣርቶ ቀርቦ ፍትሓዊ ፍርድ በመሰጠት ህብረተሰቡ እንዲማርበት እየተደረገ ይገኛል፡፡ተጥለው የተገኙ ህፃናትን ከተለያዩ NGO እና ህፃናት ማሳደጊያ ጋር በመቀራረብ ተወስደው እንዲያድጉ እየተደረገ ነው፡፡የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ህፃናትንም እንዲሁ ከተለያዩ አካላለት ጋር በቅንጅት በመስራት እንዲረዱ እየተደረገ ነው፡፡ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በተለያየ ምክንያት ተጋጭተው ከቤተሰብ ጠፍተው ለችግር የተጋለጡትንም ከሌሎች ሴክተሮች ጋር በትብብር በመስራት ወደ ቤተሰባቸው እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
ይህ የስራ ሂደት በሴቶችና ህፃናት ላይ ከመስራት በተጨማሪ በአዛውንቶችና አካል ጉዳተኞች ላይም እየሰራ ይገኛል፡፡ በልዩ ልዩ ምክንያት ጧሪ እና ተንከባካቢ ያጡ አዛውንቶች ሲቸገሩና የሚተዳደሩበት ንብረት አጥተው በሌሎች ሰዎች ሲጨቆኑና መብታቸው ሲገፈፍ ይታያል፡፡ስለዚህ ይህ ክፍል እንዲህ ያሉ ጉዳት የደረሰባቸውን አዛውንቶች ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ከጎናቸው በመቆም በመርዳት እሰፈላጊው ክብከቤ እንዲያገኙ ህጋዊ ከለላ እንዲያገኙና መብታቸው እንዲጠበቅ እያደረገ ይገኛል፡፡
በተለያየ ምክንያት አካል ጉዳተኛ የሆኑ ሰዎችን ህብረተሰባችን በኋላ ቀር ባህልና ከግንዛቤ ማጣት የተነሳ ከሰው በታችና ሰርተው ማደር እንደማይችሉ እንዲሁም አዕምሮአቸው ከሌሎች ጋር እኩል ማሰብ እንደማይችል አድርገው የሚያስቡ ነበር፡፡ ሆኖም አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ሰዎች መማርና ሊሰሩበትም የሚችሉ ናቸው፡፡
ስለዚህ ይህ የሴቶች ና ህፃናት ጉዳይ የስራ ሂደት:-