የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሥልጣን እና ተግባር
የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር የህግ አስፈፃሚ አካላትን በድጋሚ ለማዋቀር እና ስልጣናቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 163/2003 መሠረት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የሚከተሉትን ስልጣን እና የስራ ድርሻ አለው፡፡ እነዚህም፡-
1. የህገመንግስቱን ስርዓት የሚቃረኑ እና አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ማናቸውንም ተግባራትና እንቅስቃሴዎች ይከላከላል፣
2. የወንጀል ድርጊት እና የትራፊክ አደጋ እንዳይፈጠር እና እንዳይፈፀም ይከላከላል፣
3. የወንጀል ምርመራ፣ ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎችን ህጋዊና ህገመንግስታዊ መብት አክብሮ፣ ጠብቆ እንዲካሄድ ያደርጋል፣
4. በክልሉ ጥቅም እና መንግስታዊ ተቋማት ላይ ወንጀል እንዳይፈፀም ይከላከላል፣
5. የወንጀልን መነሻ በማጤን የመከላከል ስልት ያወጣል፣ ህብረተሰቡም ከወንጀል እንዲከላከል ያስተምራል፣ የተመረጡ ወንጀሎች ውጤት ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ ያደርጋል፣
6. ህብረተሰቡ የአከባቢውን ሠላም በማስከበር እና በወንጀል መከላከል ላይ እንዲሳተፍ የኮሚኒቲ ፖሊሲንግ እና የሠላም ቦርድ ያደራጃል፣ ከሚመለከተው አካል ጋር ይሰራል፣ ያስተባብራል፣

7. የክልሉን ሠላም አስተማማኝ ለማድረግ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ከፌደራል መንግስት እና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር መረጃ ይለዋወጣል፣ በቅንጅት ይሰራል፣
8. ክልሉን ለሚያቋርጡ ትላልቅ መንገዶች፣ የመንግስት ድርጅቶች፣ ድልድይ፣ ለትላልቅ ፋብሪካዎች እና የኢነቨስትመንት እንቅስቃሴዎች በሚካሄዱባቸው ቦታዎች፣ የህዝብ ስብሰባ፣ በትላልቅ በዓላት፣ለከፍተኛ ባለስልጣናት እና ወ.ዘ.ተ ጥበቃ ያደርጋል፣ ስርዓትና ደህንነት መጠበቃቸውን ያረጋግጣል፣
9. ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ አካላት ለህፃናት፣ ለሴቶች፣ አዛውንቶች እና ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት በመስጠት ይሠራል፣
10.የወንጀል መከላከልና ምርመራ ስራዎችን ለማጠናከር የፖሊስ ሞያና አገልግሎት ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፣
11. የክልሉን የፖሊስ አደረጃጀት፣ አገልግሎትና የስራ አፈፃፀም ማጤንና የኢንስፔክሽን ስራ ማካሄድ፣ የስትራቴጂክ ዕቅድ ያወጣል፣ በተመሳሳይ መልኩ ስራ ላይ እንዲውል የስራ አፈፃፀም ስልት ያወጣል፣
12. በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የጦር መሣርዎችን ይመዘግባል፣ ፍቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ይቆጣጠራል፣ በህግ ላይ ተመስርቶ ትጥቅን ያስፈታል፣
13. ከአቃቤ ህግ ጋር በመሆን የህግ ምስክሮችን ያቀርባል፣
14.የክልሉ ፍርድ ቤት ስልጣን የሆኑትን ወንጀሎች ከአቃቤ ህግ ጋር ይመረምራል፣
15. ከአቃቤ ህግ ጋር በመሆን የቴክኒክ ምርመራዎች ያካሂዳል፣ ምስክርነት ይሰጣል፣ ከወንጀል ነፃየሆነ ማስረጃ ይሰጣል፣
16.በእግዚቢትነት የተያዙ ንበረቶችን በጥንቃቄ ይጠብቃል፣ምርመራው እስኪጠናቀቅ ድረስ በአያያዛቸውና ለባለቤታቸው ስለሚመለስበት ሁኔታ ከአቃቤ ህግ ጋር ይሰራል፣ ምርመራው ሲጠናቀቅ ለማስረጃነት የሚያስፈልጉትን ለፍርድ ቤት ያቀርባል፣ እንዲሁም በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎችን ንብረት በአደራ ይይዛል፣አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ይመልሳል፣
17. ከፍርድ ቤት የሚሰጥን ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ ይፈፅማል፣
18.የወንጀል ምርመራና የትራፊክ አደጋ መዝገቦችን እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ከአቃቤ ህግና ከሚመለከተው አካል ጋር በስርዓት እንዲጠበቁ ያደርጋል፣
19.ድንገተኛ አደጋ ሲከሰት እንደየተፈጠረው አደጋ ሁኔታ እርዳታና ድጋፍ ይሰጣል፣ ከሚመለከተው አካል ጋር በትብብር ይሰራል፣
20.ለክልሉ ፖሊስ አስፈላጊውን የሰው ኃይል መልምሎ ያሰለጥናል፣ያስተምራል፣ አስፈላጊ በሆነ ቦታ መድቦ ያሰራል፣የስራ ላይ ስልጠናም ይሰጣል እንዲሰጥም ያደርጋል፣
21. የአድማ ብተና እና የተደራጁ ወንጀለኞችን መቆጣጠርያ ኃይል ያደራጃል፣ ያሰለጥናል፤ ያሰማራል፣
22.የፖሊስን የማስፈፀም ችሎታ ለማሳደግ በየጊዜው የትምህርት ዕድል ያመቻቻል፣
23.የወንጀል መረጃና እስታስቲክስ ያሰባስባል፣ ይመረምራል፣ እንደ አስፈላጊነቱ ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፣
24.የክልሉ የፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲቋቋም ያደርጋል፣ ማቴሪያልና የሰው ኃይል ያሟላል፣ያደራጃል፣ያስተዳድራል፡፡