.

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምስረታ አጭር ታሪክ

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምስረታ አጭር ታሪክ

2የኦሮሚያ ክልል ከትግራይ ክልል በስተቀር ከተቀሩት ክልሎች ሁሉ ጋር የምትዋሰን ሲሆን የመሬት ስፋቷ 363,136 እስኩዌር ኪሎ ሜትር የሆነ፣ በ 20 ዞኖች፣ 16 የከተማ መስተዳድሮች፣ 349 ወረዳዎች እና 7,262 ቀበሌዎች ፡የተዋቀረች እንዲሁም፡ ከ 35 ሚሊዮን በላይ የሆነ የህዝብ ብዛት በውስጧ የሚኖርባት ናት፡፡ ስለ ክልላችን ይህን ያህል ካልን ወደዚህ ፅሑፋችን ዋናው መነሻ ሐሳብ አብረን እንሸጋገር፡፡ መልካም ንባብ!

የክልሉ ፖሊስ በሀገሪቷ እና ክልሉ ህገመንግስት ላይ በመመስረት የክልሉን ሠላም እና ፀጥታ በማረጋገጥ የህግ የበይነትን አክብሮ በማስከበር የክልሉ ህዝብ በሠላም ወጥቶ እንዲገባ፣ የዕለት ኑሮውን ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር እንዲያጣጥም ለማድረግ ጥቅምት 1985ዓ.ም በአዋጅ የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ የያዘውን ህዝባዊ ዓላማ

የኦሮሚያ ፖሊስ የያዘውን ህዝባዊ ዓላማ ከግብ ለማድረስ ለመጀመሪያ ጊዜ 5,152 የሰው ኃይል፣ 7 ተሽከርካሪዎችን እና 7 የግንኙነት ሬዲዮችን ብቻ ይዞ ነበር ወደ ስራ የገባው፡፡ ከክልሉ ስፋት እና የህዝብ ብዛት አንፃር ያለው የፖሊስ ኃይል እና ሎጂስቲክ የያዘውን ግብ ለማሳካት በቂ ስላልነበር እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ውስብስብ በሆነ ሁኔታ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በመከላከል የክልሉን ሠለም በቀጣይነት እውን በማድረግ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከጊዜ ወደ ጌዜ በሂደት የአባላቱን እና አመራሩን አቅም በብዛትም ሆነ በሙያዊ ብቃት ማጠናከር እና ለዚህ ሥራ የሚያስፈልጉ ዘመናዊ መሣሪያዎችን ማሟላት ጀመረ፡፡

በዚሁ መሠረት የሰው ኃይል በማፍራቱ ረገድ በ1985ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በጂማ እና አዳማ ከተማ በዛፍ ጥላ ስር ከጥቂት ቀናት ስልጠና እስከ ወራት ለሚቆጠሩ ጊዜያት በማሰልጠን አዳዲስ አባላት ማፍራት የጀመረው የክልሉ ፖሊስ ከጊዜ ወደ ጊዜ ውስጣዊ ኃይሉን እያጠናከረ በመምጣቱ በአሁኑ ወቅት የአንድ ፖሊስ ማሠልጠኛ ማዕከል እና የአንድ ፖሊስ ኮሌጅ ባለቤት በመሆን ከ1ኛ እስከ 24ኛ ዙር የመደበኛ ፖሊስ አባላትን  በሠንቀሌ ኦሮሚያ ፖሊስ ማሠልጠኛ ማዕከል እና ለገ ዳዲ እንዲሁም ዲፕሎማ እና ከዚያ በላይ ያላቸውን ከህብረተሰቡ ውስጥ በመመልመል በኮሚኒቲ ፖሊሲንግ ኦፊሰር ለአንድ ዙር በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ሰልጥነው ወደ ሥራ እንዲሰማሩ በማድረግ አቅሙን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠናከረ መጥቷል፤ በአሁኑ ጊዜም ለሁለተኛ ጊዜ የዲፕሎማ መኮንኖችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡

አባላትን በብዛት ማፍራት ብቻውን ከተቋሙ የሚፈለገውን ውጤት መምጣት ስላላስቻለ በቂ ችሎታ እና ብቃት ይዘው

በሌላ በኩል ደግሞ አባላትን በብዛት ማፍራት ብቻውን ከተቋሙ የሚፈለገውን ውጤት መምጣት ስላላስቻለ በቂ ችሎታ እና ብቃት ይዘው ከህብረተሰቡ የወጡ እስከ ህይወት መስዋዕትነት በመክፈል በፍትህ እና በብቃት ማገልገል የሚችሉ  አባላት እና አመራሮችን ለመፍጠር የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎችን በክልልም ሆነ በፌደራል ፖሊስ ደረጃ እንዲያገኙ በማድረግ እንዲሁም በርካታ አባላት ከሠርተፍኬት እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ በተለያዩ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ዕድል አግኝተው እንዲማሩ በማድረግ በመናዊ ክህሎት እና እውቀት በማጎልበት እንዲሁም ህብረተሰቡ የኔ ብሎ አምኖ በመቀራረብ አብሮ መስራት የሚችል ፖሊስ ለመፍጠር በተሰራው ሰፊ ስራ ስኬታማ መሆን ተችሏል፡፡

በሎጂስቲክም ሆነ በተሟሉት አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዕቃዎች በመታገዝ ለመስራት

በዚሁ መሰረት የተለያዩ ዘመናዊ ዕቃዎችን በተመለከተ በሚያስፈልገው ልክ ሙሉ በሙሉ ተሟልቷል ለማለት ባይቻልም በሎጂስቲክም ሆነ በተሟሉት አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዕቃዎች በመታገዝ ለመስራት የመንግስት አቅም እስከቻለ ድረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ በግዢ እና በድጋፍ እየተሟላ በመምጣቱ በአሁኑ ጊዜ ከቀድሞ የበለጠ መሻሻል አለ ለማለት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ፡- የቴክኒክ ምርመራ የሚደረግበት እንደ ሰነድ ምርመራ፣ የእሳት ቃጠሎ፣የጦር መሣርያዎች እና የተለያዩ የፎረንሲክ ላብራቶሪ መሣርያዎች በ9,412,532.00 ብር በመግዛት ከዚህ በፊት በፌደራል ፖሊስ ብቻ ይደረግ የነበረን ምርመራ በክልላችንም እንዲተገበር ማድረግ በመጀመሩ ቀደም ሲል የዘህን ምርመራ ውጤት ለማግኘት ብዙ ወራት ይወስድ የነበረው በሁለት እና ሶስት ቀናት ውስጥ እየተጠናቀቀ መሆኑን ማንሳት ይቻላል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሎጂስቲክ ከየት ወዴት?

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሎጂስቲክ ከየት ወዴት?

ቀጣይነት ያለው አስተማማኝ ሠላም በማረጋገጥ የህግ የበላይነትን ለማስከበርና የአንድን ሀገር ፈጣን ልማት በማሰመዝገብ ውስጥ የሎጂስቲክ ሚና ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡የኦሮረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ1985 ዓ.ም ተመስርቶ ከክልል እስከ ወረዳ ጣቢያ መዋቅር በመዘርጋት 5152 የሰው ኃይል፣7 አሮጌ ኋላ ቀር መኪኖችና 7 የግንኙነት ሬዲዮዎችን ብቻ ይዞ ነበር አገልግሎት የጀመረው፡፡

እንደ ክልሉ ስፋትና የህዝብ ብዛት የነበረው የፖሊስ ኃይልና ሎጂስቲክስ በቂ ስላልነበር በተለያየ ምክንያት ውስብስብ በሆነ ሁኔታ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በመከላከል የክልሉን ሠላም ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ለማረጋገጥና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የነበረው ችግር ቀላል አልነበረም፡፡

የአባላቱንና የአመራሩን አቅም በብዛትም ሆነ በሞያዊ ብቃት ማጠናከር

ስለዚህ ኮሚሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ቀስ በቀስ የአባላቱንና የአመራሩን አቅም በብዛትም ሆነ በሞያዊ ብቃት ማጠናከርም ሆነ ለዚህ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን ለማሟላት ህብረተሰቡ፣ ባለ ሀብቶችና  የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰጣው ትኩረት በቂ የሆነ በጀት ተመድቦ በሎጂስቲክ በኩል ያለው እጥረትና  ችግሮች በተወሰነ መልኩ መፍትሔ እያገኘ የመጣና በተለይ በ2006 የበጀት ዓመት ጀምሮ እስከ  አሁን 2009 ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ዘመናዊ ተሸከርካሪዎች በብዙ ቢሊዮን ብር ተገዝተው ለሚያስፈልገው አገልግሎት እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

በዚሁ መሠረት አመፅ ወይም አድማን ለማክሸፍ የሚያገለግል ዘመናዊ መኪና ተገዝቶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን እና የተለያዩ መኪናዎችን ከኮሚሽን አንስቶ እስከ ወረዳዎች ድረስ ለማሟላት ያለው ጥረት አበረታች ነው፤ በተይም ከ2006 እስከ 2007 የበጀት ዘመን ውስጥ የክልሉ መንግስት ለፖሊስ ኮሚሽኑ ጥያቄ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በምላሹም ከዘመኑ ጋር የሚሄዱ የተለያዩ ዘመናዊ መኪናዎች ተገዝተው በኮሚሽኑ እጅ ገብተዋል፡፡የትራፊክ አደጋን ለመቀነስም ግንዛቤ ከመፍጠሩ ስራ በተጓዳኝ በዘመናዊ መሣርያ የታገዘ ቁጥጥርን  ማጠናከር አስፈላጊ ስለሆነ የፍጥነት መቆጣጠርያ ራዳር እና ጠጥተው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር አልኮል ቴስተር በተውሰኑ የትራፊክ አደጋ የሚበዘባቸው ዞኖች እና ከተሞች ውስጥ ስራ ላይ እንዲውል ሆኗል፤ በሌሎች ቦታዎችም እንዲስፋፋ ታስቧል፡፡ 

መረጃ በፖሊስ ስራ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ስላለው

በሌላ በኩል መረጃ በፖሊስ ስራ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ስላለው ከኋላቀር የሬዲዮ ግንኙነት መሣርያዎች በመላቀቅ ዘመናዊ በሆኑ የሬዲዮ መገናኛ መሣርያዎችን መጠቀም ተችሏል፡፡ በተፈለገው አቅጣጫ የያዘውን ህዝባዊ ዓላማ ከግብ ለማድረስ  በዚህ የማያቆመው የኦሮሚያ ፖሊስ ደረጃ በደረጃ ጊዜው ከሚጠይቀው ተጨባጭ አሰራር ጋር አዛምዶ በማካሄድ ውጤታማ ለመሆን በተለያዩ አቅጣጫዎች ስኬታማ ያደረጉትን በርካታ ስራዎች ሰርቷል፤ እየሰራም ይገኛል፡፡   

ለሀገሪቷ የሚያስፈልገውን ልማት፣ ዲሞክራሲ እና ዕድገት

ለሀገሪቷ የሚያስፈልገውን ልማት፣ ዲሞክራሲ እና ዕድገት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ለማሳካት ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ ፈፅሞ የማይቻል መሆኑን ቀድሞ ስለተገነዘበ ከዞን አንስቶ እስከ ቀበሌዎች ድረስ የማህብረተሰብ ፖሊስን (ኮሚኒቲ ፖሊሲንግ) ስራ ላይ በማዋል የተለያዩ የክልሉ ህብረተሰብን በቡድን፣ በጎጥ እና በቤት ለቤት የሠላም ቦርድ እና በሠላም ሠራዊት በማደራጀት የወንጀል መከላከል እና የትራፊክ ደህንነት ትምህርት በመስጠት ግንዛቤ በመፍጠር በተለይ የሐይመኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በዚህ ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወቱ በማድረግ ህብረተሰቡ ራሱ ባለበት ቦታ ውንጀልን ተጠይፎ ቀድሞ በመከላከል የአከባቢውን ሠላም እንዲያስከብር እና ከትራፊክ  አደጋ እራሱን እንዲጠብቅ በመደረጉ ስኬታማ መሆን ተችሏል፡፡

የወንጀልን መነሻዎች በመለየት ከምንጩ ለማድረቅ

 የወንጀልን መነሻዎች በመለየት ከምንጩ ለማድረቅ ከተሰሩት ስራዎች መካከል እንደምሳሌነት ሳይጠቀስ የማይታለፈው በወንጀል ተግባር ለይ ተሰማርተው የነበሩ ወጣቶችን በማደራጀት ወደ ስራ ተሰማርተው ወንጀልን እንዲከላከሉ ከማድረግ ጎን ለጎን ራሳቸውን ችለው የራሳቸው ሥራ ባለቤት ሆነው በሀገሪቷ ልማት ውስጥ ድርሻቸውን እንዲወጡ ለማድረግ የተሰራው ስራ የህብረተሰቡን ተሳትፎ በእጅጉ ከፍ ያደረገ ተግባር ነው፤ በዚህም ምክንያት የተገኘው ውጤት ህብረተሰቡ ከምንጊዜውም በላይ በትራፊክ አደጋ እና ወንጀል ዙርያ ያለው ግንዛቤ በመጨመሩ ያለ አንዳች ፍርሃት ወንጀለኞችን በማጋለጥ፣በመጠቆም እና ምስክር መሆን ጀምሯል እንዲሁም  ህዝቡ ከፖሊስ ጋር ለመስራት ያለው ፍላጎት የፖሊስና ህብረተሰቡ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን ያረጋግጥልናል፡፡

በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ወንጀልንና የትራፊክ አደጋን ከመከላከል

 በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ወንጀልንና የትራፊክ አደጋን ከመከላከል አልፎ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸውን ሰዎች መርዳት መጀመሩ ህብረተሰቡ በራሱ የፖሊስ ጣቢያን መገንባት እና አስፈላጊ የሆኑ ማቴሪያሎችን ማሟላት መጀመሩ ከተገኙት ውጤቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በተጨማሪም የኦሮሚያ ፖሊስ በድርጅቱ ውስጥ በአድሎ፣በትውውቅ፣በዝምድና መስራት እና የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና አሰራርን በመታገል እና ኋላቀር አሰራርን በማስቀረት በመዋቅሮቹ ውስጥ መልካም አስተዳደርን በመዘርጋት ለደንበኞቹ የተቀላጠፈና ግልፅነት የተሞላበት አገልግሎት ለመስጠት የተለያዩ ማሻሻያዎች(ሪፎርም) እንደ ሲቪል ሰርቪስ፣ መሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ(BPR)፣ ውጤት ተኮር የምዘና ስርዓት(BSC) እና የሠላም ሠራዊት(አንድ ለአምስት)ስራ ላይ በማዋል የአባላትን ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ በማጠናከር የተሰራው ስራና እየተሰራ ያለው አበረታች ነው፡፡ ይህም የፖሊስና ህብረተሰቡ ግንኙነት በጥሩ ሁኔታ አየተጠናከረ እንዲመጣ አድርጓል፤ባለጉዳይ ያለ አንዳች መመላለስ ጉዳዩን ወዲያው አስጨርሶ በሚሰጠው አገልግሎት እንዲደሰት እየተደረገ ነው፡፡ በምርመራ በኩልም እጅ ተፍንጅ የተያዙ ወንጀለኞች ወዲያውኑ በ’’RTD” ህጋዊ ቅጣት እንዲያገኙ በመደረጉ ወንጀል ፈፃሚዎች ከወንጀል ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ ተችሏል፣ አቃቤ ህግና መርማሪ ፖሊስ አንድላይ እንዲመረምሩ በመደረጉ ባለጉዳይ እንዳይመላለስ አድርጓል፡፡

የክልሉን ሠላምና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ

የክልሉን ሠላምና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በበለጠ ከህብረተቡና ከሌሎች የደህንነት አካላት ጋር በቅንጅት ጠንክሮ እየተሰራ ነው፡፡ መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋፋትና ግንዛቤ በመፍጠር በኩልም ጥሩ ሥራዎች ተሰርተው ለዕውቀት፣ ለማስጠንቀቅያነትና ለመልካም ተሞክሮ የሚሆኑትን በመለየት በተለይ በህትመቱ ሚዲያ በመጼት፣ ብሮሸርና ፓምፕሌት ወዘተ በኩል እንዲሁም በኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን በመጠቀም በማሰራጨት በተጨማሪም ህዝባዊ በዓላትን አብሮ በማክበር በዛውም ወቅታዊ የመንግስት መልዕክት በማስተላለፍና የህዝብ ውይይት ሲካሄድ በመገኘት የአንዱን ዞን መልካም ተሞክሮ ወደ ሌላው በማስፋፋት የተሰራው ሥራ የህዝብን ተሳትፎ በማጠናከር ወንጀልን የሚጠላ፣ የሚከላከል ማህበረሰብ በመፍጠር ከፖሊስ ጎን ተሰልፈው ድርሻቸውን እንዲወጡ በማድረግ ውጤታማ መሆን ተችሏል፡፡

ስራዎቻችን

ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ

ወንጀል መከላከል

የወንጀል ምርመራ

የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ

ትራፊክ

Go to top