የትራፊክ ወንጀልና አደጋን በጋራ እንከላከል!
በኢትዮጵያ ወንጀለኛ ህግ አንቀፅ 23 ቁጥር 1ላይ እንደተጠቀሰው ወንጀል ማለት ጥፋት ወይም ወንጀል በሚፈፅሙ ሰዎች የሰው ህይወት፣ ንብረትና መንግስት ላይ የሚደርስ ጉዳት/አደጋ ነው፡፡ ንብረት ስንል የተፈጥሮ፣ ሕይወት ያላቸው፣የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ማለት የቻላል፡፡ወንጀል መከላከል ማለት ደግሞ አንደ ወንጀል ከመከሰቱ በፊት ጥናት በማካሄድ ከህብረተሰቡ በሚገኝ መረጃ መሰረት መረጃን መተርጎም፣ማደራጀት፣ የአፈፃፀም አቅጣጫ በመስቀመጥ ሊፈፀም ታስቦ የተደራጀን ወንጀል ሳይፈፀም ማክሸፍ፣መከላከል ወይም ማስቀረት መቻል ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ወንጀል መከላከል ማለት የወንጀል ተግባር መከላከል ዘዴ(አካሄድ) ሲሆን እንደ ፖሊስ ስናየው የወንጀል መከላከል ስራ የሚሰራው ህብረተሰቡን በስፋት በማሳተፍና ከደህንነት አካላት ጋር በመቀናጀት ከህብረተሰቡ በተገኘ መረጃ መሰረት ሊፈፀም የታሰበን ወንጀል መከላከል ማለት ነው፡፡
ወንጀልን መከላከል የሚቻለው ሁሉም ህብረተሰብ ወንጀል በመንግስት፣ህይወትና ንብረት ላይ የሚያመጣውን ጉዳት በመገንዘብ በወንጀል መከላከል ስራ ላይ በስፋት መሳተፍ ከቻለ ነው፡፡ስለዚህ ወንጀል በህብረተሰቡ፣በፖሊስና በሁሉም የህብረተሰቡ እርከን ሲሆን ወንጀልን በመከላከል የህብረተሰቡ ድርሻ ከፈተኛና መተኪያ የሌለው ነው፡፡
ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር ካልሆነ በስተቀር ወንጀልን መከላከል አይችልም፡፡ ወንጀልን እንዴት መከላከል ይቻላል የሚለውን ካየን በወንጀልና ሊደርስ በሚችለው የትራፊክ አደጋ ላይ ምርምር በማድረግ ለወንጀል የተጋለጡ ቦታዎችና ወንጀል የሚፈፀምባቸው ተለይተው ፖሊስ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ወንጀልና አደጋን ይከላከላል፡፡

ወንጀልንና ትራፊክ አደጋን በመከላከልና መቆጣጠር ላይ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነወው፡፡ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ ወንጀልንና የተራፊክ አደጋን መከላከል ፈፅሞ አይቻልም አይታሰብምም፡፡ ወንጀልን መከላከል ካልተቻለ የህግ የበላይነት አይከበረም፤በሰዎች ህይወት፣ንብረትና በመንግስት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ይበራከታል በተመሳሳይ የተራፊክ አደጋም ይበራከታል፡፡ህግ ይጣሳል፣ዲሞክራሲ አይኖርም፣ ኢኮኖሚውና ልማት ይወድቃል፣ የሀገርና የመንግስት መኖር ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ በሁሉም አቅጣጫ በህገወጥ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ይበዛሉ፡፡ ህጋዊ የሆኑ ግለሰቦች ቦታ ያጣሉ፡፡ በሠላም ወጥቶ መግባት፣ ሰርቶ ማደርና መኖር ይቀራል፡፡ በተለይ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርስ ወንጀል ይባባሳል፣ ድህነት ይስፋፋል፣ ዲሞክራሲ፣ ልማትና የሀገር ብልፅግን ማሰብ አይቻልም፣ አይኖርም፡፡ለዚህ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከምስረታው ጀምሮ ህገ-መንግስቱን አክብሮ ማስከበር ድርሻ በመውሰድና ያለበትን የህግ የበላይነት የማስከበር ኃላፊነትን ለመወጣት ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን የፖሊስ አባላትና አመራሮች ዲሞክረሲያዊና ሀገራዊ አመለካከት አዳብረው የህዝቡ ጋሻ ሆነው መስራት እንዲችሉ በማሰልጠንና የፖሊስ ሳይንስ በማስተማር የተጣለበትን የመንግሰትና የህዝብ አደራ ኃላፊነት ለመወጣት ጠንክሮ አየሰራ ነው፡፡
አስተማማኝ ሠላምና ደህንነትን በማረጋገጥ የዲሞክራሲ ግንባታ፣ ልማትና የሀገር ዕድገትን ለማፋጠን የሰፊው ህብረተሰብና የፖሊስ በቅንጅት መስራት ተጠናክሮ መሰራት አለበት የሚለው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መልዕክት ነው ፡፡